ስለኛ
AHEAD ከድርጅትም በላይ ነው። ወደ ብሩህ ተስፋ ሚወስድ እንቅስቃሴ ነው።
የቆምንለት አላማ
እኛ የምንሰራው ግለሰቦችን እና ማህበረሰቦችን ለማብቃት ጊዜያዊ መፍትሄዎችን ለማቅረብ ሳይሆን በትምህርት እና በፈጠራ ስራ ዘላቂ ለውጥ ለመፍጠር ነው። በዘላቂ ልማት ላይ በማተኮር፣ ፕሮጀክቶቻችን ከተቋቋሙ ከረጅም ጊዜ በኋላ ቀጣይነት ያለው ለዉጥና በምንደግፋቸዉ ማህበረሰቦች ዉስጥ ጥልቅ የሆነ የአካባቢ ሃላፊነት እና የመቋቋም ስሜት እንዲኖር ማድረግን ማረጋገጥ ነው ።
ታማኝነት እና ግልጽነት በስራችን ወሳኝ ናቸው። ግልጽ እና ታማኝ አጋርነቶችን እናከብራለን እናም ያለንን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም፣ እያንዳንዱ ጥረት ከተልዕኳችን ጋር የሚጣጣም እና የተጠያቂነት የሚያከብር እንዲሆን እንሰራልን።
ፈጠራ ለዕድገታችን አጋዥ ነው። በፈጠራ፣ የተበጁ መፍትሄዎችን በመጠቀም፣ ውስብስብ ችግሮችን በአዲስ እይታዎች እንፈታልን። የዲጂታል ትምህርትን ከማሳደግ ጀምሮ በዘላቂ የግብርና ልምዶች፣ ሰዎች ተግዳሮቶችን እንዲያሸንፉ እና ሙሉ አቅማቸውን እንዲጠቀሙ የሚያስችላቸውን መንገዶችን መፍጠር።
አሄድ ከድርጅትም በላይ ነው። ወደ ብሩህ፣ እና ፍትሃዊ ነገ የሚደርግ ጉዞ ነው።
"ትምሀርት አለምን ለመቀየር የምንጠቀምበት ትልቁ መሳርያ ነው!"
~ Nelson Mandela
ራዕያችን
ወደፊት ሰዎች በብልጽግና ፣ በእውቀት፣ ሀብት እና በፈጠራ የተለያዩ እድሎችን የሚያገኙበት ነገን መገንባት ነው። ሁሉም ሰው የራሱን መንገድ ለመቅረጽ፣ ጠንካራ ማህበረሰቦችን ለመገንባት እና ለማደግ እድል በማመቻቸት እናምናለን።
ተልዕኳችን
በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ማህበረሰቦችን በዘላቂ ልማት፣ ትምህርት እና ፈጠራ ማጎልበት ነው። የዲጂታል ትምህርት ተደራሽነትን በማቅረብ፣ ኃላፊነት የሚሰማው የመሬት አስተዳደርን በማጎልበት እና የአካባቢ ተነሳሽነቶችን በመደገፍ ዘላቂ ለውጥን ለመፍጠር ቆርጠን ተነስተናል። ወዳጅነትን በመገንባት እና የአካባቢ እውቀትን በመቀበል ግለሰቦች እና ማህበረሰቦች እንዲበለፅጉ እና የራሳቸውን የወደፊት ጊዜ እንዲቀርጹ ዕድሎችን ለመፍጠር እንጥራለን።