AHEAD Institute

ሰእል መንፈሳዊ ስብራትን ለመጠገን፡ ህይወትን በመለወጥ ትግራይን መደግፍ

AHEAD Institute, Healing Through Art

ሰእል መንፈሳዊ ስብራትን ለመጠገን፡ ህይወትን በመለወጥ ትግራይን መደግፍ

የጽናት እና የተስፋ ጉዞ

ፈጠራ የፈውስ መሳሪያ የሚሆንበትን እና የኪነጥበብ ሃይል  የተመሰቃለ ህይወትን የሚገነባበትን ቦታ አስቡት። ስሜ አና አምፍት ይባላል፣ ኢትይጲያ ሁለተኛ ቤቴ ናት። በኢትዮጵያ ከሁለት አመት በላይ ኖሪያለሁ እዚያ በነበርኩበት ወቅት ወደተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች መጓዝ ችያለሁ። ከተጓዝኩባችሀውም ቦታዎች መካከል  ከጦርነት የወጣው ትግራይ ክልል ይገኝበታል። በትግራይ ቆይታዬ ያጋጠሙኝ ታሪኮች እና ሊታሰቡ የማይችሉ ጉዳቶች በኔ ላይ የማይጠፋ አሻራ ጥለዋል።

ዛሬ ትግራይ ትልቅ ፈተና ገጥሟታል። 81 በመቶ ወጣቶች ስራ አጥነት እና ከ2.1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ይገኛሉ፣ ነግር ግን ከነዚህ ፈታኝ ሁኔታዎች በስተጀርባ የተስፋ ጭላንጭል የሚጭሩ እንቅስቃሰዎችን መመልከት ችያለሁ። ይህ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ የመጣው በመጠን ትንሽ ነገር ግን ደማቅ ቦታ ከሆነው በመቀሌ የሚገኘው የእሴኒ አርት ጋለሪ ሲሆን ሁለቱ ድንቅ አርቲስቶች ነብዩ እና ርግበ በኪነ ጥበባቸው ህመምን ወደ ተስፋ ቀይረውታል። 

አላማቸው  ከትግራይ ጋር ካለኝ ጠንካራ ግኑኝነት ጋር በመደመር  “ሥዕል ለመንፈሳዊ ፈውስ” እሚል ፕሮጀክት እንድነድፍ መሰረት ሆኖኛል፣ ይህ ፕሮጀክት ኪን ጥበብን  ለስሜታዊ ፈውስ እና ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማምጣት መጠቀም ላይ ያተኮረ ንው።

ተልእኳችን፡ በሥነ ጥበብ ስነልቦናዊ ፈውስ ብማምጣት፣ በተግባር ማበረታታት ነው

በዚህ ፕሮጀክት በዋናነት ሁለት ተልእኮዎችን አንግበናል፡- 

ስነልቦናዊ ፈውስ፡- ስነ ጥበብን እንደ ቴራፒ በመጠቀም ግለሰቦች ከጦርነት ጉዳት እንዲያገግሙ መርዳት።

ቀጣይነት ያለው መተዳደሪያ፡ ማህበረሰቡ በንብ ማነብን የስራ መስክ እንዲሰማራ በማድረግ ቀጣይነት ያለው ሥነ-ምህዳር እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ማስጠበቅ። 

ይህ ተነሳሽነት በኢትዮጵያ ላይ በፈጠራ፣ በትምህርት እና በግብርና ላይ ዘላቂነት ያለው ለውጥ ለማምጣት በ AHEAD ኢንስቲቱት የተነደፈ ሲሆን ከተለያዩ አጋሮች ጋር በመሆን ወደተግር ለመቀየር ይሰራል።

ኪነ ጥበብ እንዴት ፈውስን ያመጣል?፡ በኪነ ጥበብ ስነልቦናዊ ስብራትን ማከም

በመቀሌ ከተማ ለሁለት ሳምንት በተካሄድው የሥዕል ስልጠና ላይ ተሳታፊዎች በስነ-ጥበብ የስሜት ስብራትን ለማከም እና ከስነልቦናዊ ስብራት ለማገገም ስዕልን እንደ መፍትሄ ተጠቅመውበታል።  ስልጠናው ማእከል ያደረግው የንብ ማነብ ጭብጥ ላይ መሰረት አድርጎ የነበረ ሲሆን ይህም የትብብር እና የዘላቂነት ምልክትን ለማሳየት ያለመ ንበር።

ንቦች መጠናቸው አነስተኛ ቢሆንም፣ የሚያስደንቅ ጥንካሬ እና አንድነት አላቸው። በአንድነት አብረው ይሰራሉ፣ እያንዳንዳቸው ቀፎቸውን በመጠበቅ እና አካባቢን በመደገፍ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። ይህ ትብብራቸው እና ትጋታቸው ከጉዳት ለማገገም  እንደ መልካም ምሳሌ ማሳያ ሆኖ ሊወሰድ ችሏል፡ ልክ እንደ ንቦች ግለሰቦች እና ማህበረሰቦችም ከዓላማ እና ከጽናት ጋር ሲገናኙ ተስፋን እንደገና  መገንባት፣ ማደግ እና አወንታዊ ውጤት መፍጠር ይችላሉ። 

በንብ ማነብ ሃሳብ ላይ መሰረት አርጎ በተካሄድውአውደ ርዕይ ላይ ተሳታፊዎች ንቦች የአካባቢ ጥበቃላይ የሚጫወቱትን ወሳኝ ሚና አንጸባርቀዋል ። እነዚህ የአውደ ራይ ጊዜዎች የፈጠራ ልምምዶች ብቻ አልነበሩም;ይልቁንም  ከተጋላጭነት  ወደ ማገገም እና ወደ ጥንካሬ የሚደረገውን ጉዞ እና የእርስ በርስ ግንኙነት እና መደጋገፍ አስፈላጊነትን ያንጸባረቁም ነበሩ. 

በወቅቱ የስእል ዐውደርዕ ከዐውደርዕነቱ በተጨማሪ፣ የሰዎችን የተጎዳ ስሜት ለማከም ረድቷል። ከዚህ በተጨማሪም ይህ ፕሮግራም  የንብ ማነብ ስራ ለትግራይ (Beekeeper Entrepreneurs of Tigray (BET)) የተሰኘ ፕሮግራም ጅማሮ ሆኖም አልፏል።

BET ለትግራይ ወጣቶች የንብ ማነብ የስራ መስክ ላይ የቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠትና የመሰረታዊ ንብ ማነብ ቁሳቁሶችን ለመስጠት አልሞ የተነደፈ ሲሆን BETን ፕሮጀክትን የተለየ እና ውጤታማ የሚያደርገው የዲጂታል ትምህርትን በአካል ከሚሰጥ የስልጠና ጋር በማጣር የተግባር እና የንድፈ ሃሳብ ትምህርቶችን በአንድ ላይ ለመስጠት የተዘጋጀ መሆኑ ነው። ተነሳሽነቱ ሥራ አጥ ወጣቶችን አስፈላጊ የንብ ማነብ ክህሎት በማስታጠቅ የራሳቸውን ዘላቂ የንግድ ሥራ እንዲጀምሩ ያስችላቸዋል።

 

ይህንን ፕሮጀችት የበለጠ ለመደገፍ በሥዕል ትምህርት ወቅት የተሰሩት የሥዕል ሥራዎች ለግዢ ቀርበዋል፣ ገቢው በቀጥታ ለ BET ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ለመስጠት የሚውል ሲሆን ይህም ተሳታፊዎች ሁለንተናዊ ስልጠና እንዲያገኙ እና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማምጣት ያስችለናል። ይህም ሂደት ጥበብን እና ትምህርትን በዘላቂነት በማዋሃድ  ተግባራዊ ክህሎቶችን ማዳበር ብቻ ሳይሆን የታደሰ የዓላማ እና የባለቤትነት ስሜትን ለመፍጠር ያግዛል።

 

በዚህ መንገድ ተሳታፊዎች ለአካባቢ ተሃድሶ አስተዋፅዖ ያደርጋሉ፣ ዘላቂ መተዳደሪያን ያዳብራሉ፣ እና ንቦች የሚወክሉትን ፅናት እና መተባበር በማሳየት የመንፈስ የፈውስ እና የመተባበር ስሜትን ያዳብራሉ።

የአውደ ርዕይ ውጤት፡ ከሥነ ጥበብ ወደ ተግባር

የአውደ ርዕይ ተፅዕኖ በዎርክሾፖች አያበቃም. በጊዜው የተሰሩት የጥበብ ስራዎች ለዕይታ እና ለሽያጭ ቀርበዋል፣ ገቢው እንደገና ወደ ማህበረሰቡ ገብቷል። ይህ ሞዴል ግላዊ ማገገምን በኪነጥበብ በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ እድገትን ማጎልበት ጋር በማጣመር ቀጣይነት ያለው የድጋፍ ሂደትን ለመፍጠር ያስችለናል።

የስነጥበብ ህክምናን ከዘላቂ ልምምዶች ጋር በማጣጣም ግለሰቦች እንዲፈውሱ ብቻ ሳይሆን የትግራይ ማህበረሰቦችን ኢኮኖሚያዊ መዋቅር ለማጠናከር የረዳናል።

የእርስዎ ድጋፍ ለምን ያስፈልገናል?

ማንም የተወለደበትን ቦታ አይመርጥም, ነገር ግን ሁላችንም ለውጥ ለማምጣት መምረጥ እንችላለን. ዓለምን ብቻችንን መለወጥ ባንችልም አንድ ላይ ሆነን ዘላቂ ተፅዕኖ መፍጠር እና  ድጋፋቺን ለሚያስፈልጋቸው መድረስ እንደምንችል አምናለሁ። 

ትንሽም ይሁን ትልቅ የእርስዎ አስተዋጽዖ ያግዘናል!

የርሶ ድጋፍ፡  

  • እንደ የስዕል ሸራዎች፣ ብሩሾች እና ቀለሞች ያሉ አስፈላጊ የጥበብ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ ያግዘናል።
  •  ቴራፒስቶች እና ዎርክሾፕ አስተባባሪ ባለሞያዎች ወጪዎችን ይሸፍንልናል።
  • በአዲስ አበባ ውስጥ ለምናካሂደው አውድውርእይ የሥዕል ሥራዎችን ከቦታ ቦታ ልማጓጓዝ ያግዘናል። 

እነዚህ አውድውርእዮች ገንዘብ ማሰባሰብ ብቻ ሳይሆኑ ስለ ትግራይ ነባራዊ ተግዳሮቶች እና የንብ እርባታ ጥቅም ግንዛቤን ለመፍጠር እንጠቀማቸዋለን።

እንዴት መሳተፈ ይችላሉ?

ህይወትን ለመቀየር ይቀላቀሉን:  

➡️ Donate: Your contribution directly funds painting workshops and supports community-focused projects.  

➡️ Partner with Us: Collaborate on innovative projects and help expand our reach.  

➡️ Volunteer: Share your skills and make a hands-on impact in Tigray.  

Leave a Comment

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

Scroll to Top